Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

Available in 54 languages
«ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ጉንጩን የመታ፣ አንገትያውን የቀደደ፣ በድንቁርና ጥሪ የተጣራ ከኛ አይደለም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንዳንድ የድንቁርና ዘመን ሰዎች ተግባር አስጠነቀቁም ከለከሉም። እንዲህም አሉ: እነዚህ ከኛ አይደሉም: የመጀመሪያው: ጉንጩን የመታ ነው። ጉንጭን የለዩት በአብዛኛው የሚፈፀመው እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተቀሩትን የፊት ክፍልን መምታትም ክልከላው ውስጥ ይካተታል። ሁለተኛው: ልብስ ላይ ጭንቅላት እንዲገባበት ተብሎ የሚከፈተውን (አንገትያ) ከትእግስት ማጣት ብዛት መቅደድ ነው። ሶስተኛው: የድንቁርና ዘመን ጥሪዎችን መጣራት ነው። ለምሳሌ ያህል፦ ወዮልኝ፣ ወይኔ በጠፋው ማለት፣ ሙሾ ማውረድ፣ እየገጠሙ ማለቃቀስና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality