ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች
ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከዕብ ቢን ዑጅራህ አገኘኝና እንዲህ አለኝ: 'ስጦታ ላበርክትልህን?
Available in 60 languages
«ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከዕብ ቢን ዑጅራህ አገኘኝና እንዲህ አለኝ: 'ስጦታ ላበርክትልህን? ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው? እርሳቸውም፦ ‹አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ፤ አልላሁመ ባሪክ ዓላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ። በሉ› አሉን።'" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ውዳሴህን ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው፤ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው ረድዔትን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸውም ረድዔትን አውርድላቸው፡፡ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡”)»Meaning translation ·
Saved at original quality








