Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

የበኒ ሙጃሺዕ ወንድም ከሆነው ከዒያድ ቢን ሒማር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከልም:

Available in 40 languages
«የበኒ ሙጃሺዕ ወንድም ከሆነው ከዒያድ ቢን ሒማር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከልም: "አንዱ በአንዱ ላይ በማይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን በማይተላለፍበት ልክ እንድትተናነሱ አላህ ወደኔ ራዕይ አውርዷል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለባልደረቦቻቸው ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው መካከልም: አላህ እንዲህ ብሎ ራዕይ ማውረዱን ተናገሩ: ሰዎች በዘራቸው ወይም በገንዘባቸው ወይም ከዛ ውጪ ባሉ ነገሮች አንዱ በአንዱ ላይ ልቅናን፣ ኩራትንና ክብርን ለራሱ በማድረግ ሳይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን ሳይተላለፍ ለፍጥረታት ራሳቸውን ዝቅ በማድረግና ማንነታቸውን በማለዘብ እርስ በርሳቸው መተናነሳቸው ግዴታ ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality