Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

Available in 55 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የማለ ሰው በመሀላውም 'በላትና ዑዛ እምላለሁ' ያለ ሰው 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ይበል። ለባልደረባው 'ና ቁማር እንጫወት' ያለ ሰውም ይመፅውት።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ከመማል አስጠነቀቁ። አማኝ የሆነ ሰው ከአላህ በቀር በማንም አይምልምና። ከአላህ ውጪ የማለና ለምሳሌ በላት፣ በዑዛ የማለ ሰው (እነዚህ ሁለቱ ከእስልምና በፊት በድንቁርና ዘመን ይመለኩ የነበሩ ጣዖታት ናቸው።) ነፍሱን ለማዳን ከሽርክ ለመፅዳትና ለዛ መሀላው ማካካሻ እንዲሆነው አስከትሎ "ላኢላሃ ኢለሏህ" የማለት ግዴታ እንዳለበት ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለባልደረባው "ና ቁማር እንጫወት" ያለ ሰው (ቁማር ማለት ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው አሸናፊው የሚወስደው ገንዘብ መድበው ለመሸናነፍ መጫወት ነው። ከመካከላቸውም እያንዳንዳቸው ወይ ያተርፋል ወይ ይከፍላል።) የጠራበትን ወንጀል ለማካካስ አንዳች ነገር መመፅወቱ እንደሚወደድለት ተናገሩ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality