Hadith for the World
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ

56 hadiths

56 hadiths

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ከሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: ሂሻም በሻም ውስጥ በሚገኙ ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች ፀሐይ ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ሰዎች በኩል አለፈ። እርሱም: "ምን ሆነው ነው?" አለ። ሰዎችም "ግብር ባለመክፈላቸው ለቅጣት እዚሁ ታስረው ነው።" ብለው መለሱለት። ሂሻምም «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ: "እነዚያን በዱንያ ውስጥ ሰዎችን የሚቀጡን ሰዎች አላህ ይቀጣቸዋል።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት! ወንድ ልጅ ከሌላ ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አይጠቅለል! ሴት ልጅም ከሌላ ሴት ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አትጠቅለል!"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عَن أَبي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَامَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي صَلاَةٍ وَقُمْنَا مَعَهُ، فَقَالَ أَعْرَابِيٌّ وَهُوَ فِي الصَّلاَةِ: اللَّهُمَّ ارْحَمْنِي وَمُحَمَّدًا، وَلاَ تَرْحَمْ مَعَنَا أَحَدًا. فَلَمَّا سَلَّمَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ لِلْأَعْرَابِيِّ: «لَقَدْ حَجَّرْتَ وَاسِعًا» يُرِيدُ رَحْمَةَ اللهِ.رواه البخاري
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: «إِنَّ اللَّهَ قَالَ: إِذَا ابْتَلَيْتُ عَبْدِي بِحَبِيبَتَيْهِ فَصَبَرَ، عَوَّضْتُهُ مِنْهُمَا الجَنَّةَ» يُرِيدُ: عَيْنَيْهِ.رواه البخاري
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَرَّ عَلَى صُبْرَةِ طَعَامٍ فَأَدْخَلَ يَدَهُ فِيهَا، فَنَالَتْ أَصَابِعُهُ بَلَلًا فَقَالَ: «مَا هَذَا يَا صَاحِبَ الطَّعَامِ؟» قَالَ أَصَابَتْهُ السَّمَاءُ يَا رَسُولَ اللهِ، قَالَ: «أَفَلَا جَعَلْتَهُ فَوْقَ الطَّعَامِ كَيْ يَرَاهُ النَّاسُ؟ @مَنْ غَشَّ فَلَيْسَ مِنِّي».رواه مسلم