ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች
ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
Available in 60 languages
«ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ። 'አትተሒይያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦይዪባቱ አስ‐ሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ፤ አስ‐ሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስ‐ሷሊሒን፤ አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ትርጉሙም: “ክብርና ልዕልና እንዲሁም ሶላቶችና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው፡፡ አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቶች በእርሶ ላይ ይስፈን ፤ ሰላም በእኛና በአላህ ደጋግ ባሮችም ላይ ይስፈን፤ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡”።)" በሌላ የቡኻሪና ሙስሊም ዘገባ "አላህ እርሱ ሰላም ነው። አንዳችሁ ሶላት ላይ በተቀመጠ ወቅት 'አትተሒይያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦይዪባቱ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ፤ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን' ይበል። ይህንን ያለ ጊዜ በሰማይም ውስጥ ሆነ በምድር ውስጥ የሚገኝ ደግ የአላህ ባሪያ ሁሉ ዱዓው ይደርሰዋል። ቀጥሎ 'አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' ይበል ከዚያም የፈለገውን ዱዓእ መርጦ ያድርግ!"»Meaning translation ·
Saved at original quality








