Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦

Available in 64 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመልክተኞች ሱናዎችና ከኢስላማዊ መገለጫዎች መካከል አምስቱን አብራሩ፦ የመጀመሪያው፦ መገረዝ ነው። እሱም ከወንድ ልጅ ብልት ከክርክሩ ከፍ ብሎ ያለውን ጭማሪ ቆዳና ከሴት ልጅ ብልት ደግሞ ከወንድ ብልት መግቢያ ስፍራ ከፍ ብሎ ያለውን ቆዳ ከጫፉ ቀንሶ መቁረጥ ነው። ሁለተኛው: የብልትን ፀጉር መቁረጥ ነው። ይህም ከብልት ዙሪያ ያለውን ፀጉር መላጨት ነው። ሶስተኛው: ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር: እሱም በወንድ ልጅ የላይኛው ከንፈር ላይ የበቀለን ፂም ከንፈሩ በግልፅ እስኪታይ መቁረጥ ነው። አራተኛው: ጥፍሮችን መቁረጥ ነው። አምስተኛው: የብብትን ፀጉር መንጨት ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality