Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 60 languages
«ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሽንት ወይም ከሰገራ ለመፀዳዳት ወደ ስፍራው መግባት የፈለጉ ጊዜ ከወንድ ሰይጣኖችና ከሴት ሰይጣናት ክፋት በአላህ ይጠበቁና ወደርሱም ይጠጉ ነበር። በተጨማሪ "አልኹብሢ ወልኸባኢሥ" የሚለው ቃል ክፋትና ነጃሳ ተብሎም ተተርጉሟል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality