ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
Available in 60 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): 'አሏሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወሚን ዓዛቢ‐ን‐ናር ወሚን ፊትነቲል መሕያ ወል መማት ወሚን ፊትነቲል መሲሒ‐ድ‐ደጃል' እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።" 'ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' ማለት ነው። በሙስሊም ዘገባ ደግሞ 'አንዳችሁ ከመጨረሻው ተሸሁድ ያጠናቀቀ ጊዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ: ከጀሀነም ቅጣት፣ ከቀብር ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተናና ከመሲሕ ደጃል ክፋት።'ብለዋል።"»Meaning translation ·
Saved at original quality








