Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:

Available in 48 languages
«ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ችግርና ጭንቀት በርሳቸው ላይ በሚበረታ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። "ታላቅ በሆነው" ክብሩ፣ በማንነቱ፣ በባህሪውና በድርጊቱ ነገሩ የላቀ፤ "ቻይ" ወንጀለኛን በመቅጣት የማይቸኩል ይልቁንም የሚያዘገይ፤ መቅጣት እየቻለ ይቅር የሚል፤ በሁሉም ነገር ላይም ቻይ የሆነ ነው። "ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የታላቁ ዐርሽ ፈጣሪ ነው። "የሰማያትና የምድር ጌታ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የሰማያትና ምድር ፈጣሪ፤ በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረ፤ ባለቤቱ፣ አስተካካዩና እንደፈለገው የሚያስተናብረው ነው። "የተከበረው ዐርሽ ጌታ" የተከበረውን ዐርሽ የፈጠረ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality