Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 56 languages
«ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር። በረመዷን ውስጥም በየሁሉም ምሽት ያገኛቸውና ቁርአን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአውሎ ንፋስም የበለጠ በመልካም ነገር ላይ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። ለሚገባው የሚገባውን በመስጠት ቸርነታቸው የሚበዛውም በረመዷን ወር ነበር። የቸርነታቸው መጨመር ምክንያትም ሁለት ነገሮች ናቸው: የመጀመሪያው: ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም ማግኘታቸው ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ: ቁርአንን መማማራቸው ነው። ማለትም ከቀልባቸው በሽምደዳ መቅራታቸው ማለት ነው። ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በርሳቸው ላይ የወረደውን ቁርአን ባጠቃላይ ያስተምራቸዋል። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ ቸር፣ አብዝቶ ሰጪ፣ መልካም ተግባሪና አላህ በዝናብና በእዝነት ከሚልካት መልካም ንፋስ የበለጠ ለፍጡራን ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality