ዐቂዳ (እምነት)
ከአማኞች እናት ከኡሙ ሰለማ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
Available in 39 languages
«ከአማኞች እናት ከኡሙ ሰለማ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ የተሻለ ነገር ቢተካለት እንጂ።"» ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: "አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለና?! ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ይህንን ዱዓ አልኩኝ። አላህም ለኔ የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።" ትርጉሙም ({እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} [አልበቀራ:156] አላህ ሆይ በመከራዬ ምንዳን ስጠኝ። ከደረሰበኝ መከራ የተሻለንም ተካልኝ።) ማለት ነው።»Meaning translation ·
Saved at original quality








