ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
Available in 62 languages
«ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»»Meaning translation ·
Saved at original quality







