Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦

Available in 62 languages
«ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም አላህ ዘንድ የሚመነዳው ከሙስሊሞች ጋር ከሚሰራው የስራ አይነት አንፃር እንደሆነ ገለፁ። ከአንድ አማኝ ላይ ከዱንያ ችግሮች መካከል አንድን ችግርና መከራ ያቀለለ፣ የገላገለ፣ ያስወገደና ያነሳ ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮች መካከል አንድን ችግሩን በማቅለል ይመነዳዋል። ለተቸገረ ያቀለለ፣ ያገራ፣ ችግሩንም ያስወገደ አላህም ለርሱ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ጉዳዩን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር - ለምሳሌ ግልፅ መውጣት የማይገባውን ስህተትና ጥፋት እርሱ ላይ አይቶ - የሸሸገለት ሰው አላህ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ነውሩን ይሸሽግለታል። አንድ ሰው ወንድሙን ዲናዊም ይሁን ዱንያዊ ጥቅሞቹ ላይ እስካገዘው ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ይሆናል። ማገዝ በዱዓ፣ በአካል፣ በገንዘብና ከዚህም ውጪ ባሉ ነገሮች ይፈፀማል። የአላህን ፊት ፈልጎበት ሸሪዓዊ ዕውቀትን ለማግኘት የተጓዘን ሰው ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ አላህ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ዘንድ ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በነርሱ ላይ እርጋታና ስክነት ይሰፍናል፤ የአላህ እዝነትም ይሸፍናቸዋል፤ መላዕክቶች ያካብቧቸዋል፤ አላህ ዘንድ ቅርብ ከሆኑት ጋር ያሞግሳቸዋል (ያወድሳቸዋል)። አላህ ባሪያውን በላይኛው አለም ማውሳቱ ብቻ ከክብር በቂ ነው። ስራው ጎዶሎ የሆነ ሰው የተሟላ ስራ የሰሩ ሰዎች ደረጃ ላይ አይደርስም። ስለዚህ በዘር ልቅናና በወላጆች ደረጃ ተማምኖ መልካም ስራን ማጓደል አይገባም።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality