Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 55 languages
«ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት። እርሱም "እኔ አላህና መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደዴ ውጭ ምንም ነገር አላዘጋጀሁም።" አለ። እርሳቸውም "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" አሉት። አነስም እንዲህ አሉ፦ "በዚህ "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" በሚለው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር እንደተደሰትነው በምንም አልተደሰትንም።" ቀጥሎም (አነስ) እንዲህ አሉ: "እኔ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን እወዳለሁ። እነርሱ የሰሩትን አምሳያ ባልሰራ እንኳ እነርሱን በመውደዴ ከነርሱ ጋር መሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

አንድ የገጠር ሰው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ትንሳኤ ስለምትከሰትበት ወቅት ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ: ለርሷ ከመልካም ስራ ምን አዘጋጅተህላታል? አሉት። ጠያቂውም: እኔ አላህና መልክተኛውን እወዳለሁ እንጂ ትልቅ ስራ አላዘጋጀሁላትም አለ። ከዚህ በቀር የቀልብም፣ የአካልም ሆነ የገንዘብ አምልኮ አላወሳም። እነዚህ ሁሉ ውዴታን ተከትሎ የሚመጡ ቅርንጫፎች ናቸውና። ለመልካም ስራ የሚያነሳሳውም እውነተኛ ውዴታ ስለሆነ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ: አንተ ጀነት ውስጥ ከወደድካቸው ጋር ነህ አሉት። የነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦች በዚህ ብስራት ከፍተኛ ደስታን ተደሰቱ። አነስም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቀጥሎ ስራው እንደነርሱ አምሳያ ባይሆንም እንኳ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን ስለሚወድ ከነርሱ ጋር መሆንንም ተስፋ እንደሚያደርግ ተናገረ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality