Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ:

Available in 48 languages
«ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ: "የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል።" ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ "ቀልቦችን አዘዋዋሪ የሆንከው አላህ ሆይ! ቀልባችንን በአምልኮህ ላይ አዙረው።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአደም ልጆች ሁሉ ቀልባቸው እንደ አንድ ቀልብ ከአርረሕማን ጣቶች በሁለት ጣቶቹ መካከል መሆናቸውን ተናገሩ። እንደፈለገውም ይገለባብጠዋል። ከፈለገ በሐቅ ላይ ያፀናዋል፤ ከፈለገም ከሐቅ ያጠመዋል። በሁሉም ቀልቦች ላይ የሚፈፅመው ማስተናበር የአንድ ሰውን ቀልብ እንደማስተናበር ነው። አላህን አንድ ጉዳይ ከሌላ ጉዳይ አያጠምደውም። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀጥለው ይህን ዱዓ አደረጉ "አንዳንዴ ወደ ትእዛዝህ፣ አንዳንዴ አንተን ወደ መወንጀል፣ አንዳንዴ አንተን ወደማውሳት፣ አንዳንዴ ደሞ አንተን ከማውሳት ወደ መዘናጋት ቀልቦችን የምትገለባብጥ አላህ ሆይ! ልባችንን ወደ አምልኮህ አዙረው።"

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality