Hadith for the World

All hadiths

The complete card collection, filter by chapter

655 hadiths

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሙዓዊያህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦ "አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል። እኔ አከፋፋይ ብቻ ነኝ አላህ ነው የሚሰጠው። ይህች ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ የቆመች ከመሆን አትወገድም! የአላህ ትእዛዝ እስክትመጣ ድረስም የተቃረናቸው ሁሉ አይጎዳቸውም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።"»ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
عن أنس رضي الله عنه أنه قَالَ لِثابِتٍ رحمه اللهُ: ألاَ أرْقِيكَ بِرُقْيَةِ رسولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم ؟ قال: بلى، قال: «اللَّهُمَّ رَبَّ النَّاسِ، مُذْهِبَ البَأسِ، اشْفِ أنْتَ الشَّافِي، لاَ شَافِيَ إِلاَّ أنْتَ، شِفَاءً لاَ يُغَادِرُ سَقماً».رواه البخاري
ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ثوبان رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قَالَ: "إنَّ المسلِمَ إذا عادَ أخاه المسلِمَ، لم يَزَلْ في خُرْفَةِ الجَنَّةِ حتى يرجعَ"، قيل: يا رسولَ اللهِ ما خُرْفَةُ الجنَّةِ؟، قال: "جَنَاها".رواه مسلم
عن أنس بن مالك رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم أنه كان إذا أكل طعاما، لعق أصابعه الثلاث. قال: وقال: «إذا سقطت لُقمة أحدكم فليُمِطْ عنها الأذى، وليأكلها ولا يَدَعْهَا للشيطان» وأمر أن تُسْلَتَ القَصْعَةُ، قال: «فإنكم لا تدرون في أيِّ طعامكم البركة» وعن جابر بن عبد الله رضي الله عنه أن رسولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قالَ: "إنّ الشيطانَ يَحضُرُ أحدَكُم عندَ كلِ شيءٍ من شَأنِه، حتى يَحضُرَهُ عندَ طعامِهِ، فإذا سَقطتْ لقمةُ أحدِكُم فليَأخُذْها فَلْيُمِطْ ما كانِ بها من أذى، ثم ليَأكُلْها ولا يَدَعْها للشيطانِ، فإذا فَرَغَ فليَلْعَقْ أصابعَهُ، فإنه لا يَدري في أيِّ طَعامه البركة"حديث أنس رواه مسلم. حديث جابر رواه مسلم
ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ነበርን። የ14ኛዋን ሌሊት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: ' ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም። ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለው ሶላት ላይ አለመሸነፍን ከቻላቹ አድርጉት።' ቀጥሎ ይህንን አንቀፅ አነበቡ: '{ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "የቁርአን ባለቤት የሆነ ሰው ምሳሌ የታሰረ ግመል ባለቤት አምሳያ ነው። ከተቆጣጠራት (በአግባቡ) ይይዛታል። ከለቀቃት ግን ትሄዳለች።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنسٍ رضي الله عنه : أنّهُ مَرَّ على صِبْيَانِ، فَسَلَّمَ عليهم، وقالَ: كانَ النبيُّ صلى الله عليه وسلم يَفعلُهُ.متفق عليه
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: «من عُرِضَ عليه رَيْحَانٌ فلا يرده، فإنه خفيف الْمَحْمِلِ، طيب الريح».رواه مسلم
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።"ሙስሊም ዘግበውታል።
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችው ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ 'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'"አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:- "አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!'" አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: "ቀጥለውም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه مرفوعاً: «على كل مسلم صدقة» قال: أرأيت إن لم يجد؟ قال: «يعمل بيديه فينفع نفسه ويتصدق» قال: أرأيت إن لم يستطع؟ قال: «يُعِينُ ذا الحاجة المَلْهُوفَ» قال: أرأيت إن لم يستطع، قال: «يأمر بالمعروف أو الخير». قال: أرأيت إن لم يفعل؟ قال: «يُمسك عن الشر، فإنها صدقة».متفق عليه
ከኡሳማህ ቢን ዘይድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።