Hadith for the World

All hadiths

The complete card collection, filter by chapter

655 hadiths

ከጃቢር ቢን ዓብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል። የወር መንገድ ሲቀር (ጠላቶች ውስጥ) ፍርሃት በመክተት ተረድቻለሁ፤ ምድር ለኔ መስገጃም ንፅህና መጠበቂያም ተደርጋልኛለች። ስለዚህ ከኡመቴ ማንኛውም ሰው ሶላት ከደረሰችበት ይስገድ። ምርኮ ለኔ ተፈቅዷል፤ ከኔ በፊት ለአንድም አካል አልተፈቀደችም። ምልጃ ተሰጥቶኛል። ነቢይ የሚላከው ወደ ህዝቦቹ ብቻ ነበር። እኔ ግን ወደ ሰው ባጠቃላይ ተልኬያለሁ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس بن مالك رضي الله عنه مرفوعًا: «من قال -يعني: إذا خَرج من بَيتِه-: بِسم الله تَوَكَّلتُ على اللهِ، وَلاَ حول ولا قُوَّة إِلَّا بالله، يُقَال له: هُدِيتَ وَكُفِيتَ وَوُقِيتَ، وَتَنَحَّى عَنه الشَّيطَان». زاد أبو داود: «فيقول -يعني: الشيطان- لِشَيطان آخر: كَيف لَك بِرَجلٍ قَد هُدِيَ وكُفِيَ ووُقِيَ؟».رواه أبو داود والترمذي
عن معاذ بن جبل رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم أنه قال: «قَالَ اللهُ -عَزَّ وجَلَّ-: المُتَحَابُّون فِي جَلاَلِي، لَهُم مَنَابِرُ مِن نُورٍ يَغْبِطُهُم النَبِيُّونَ والشُهَدَاء».رواه الترمذي وأحمد
ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።رواه أبو داود والنسائي وأحمد
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።› ፆም ጋሻ ነው። አንዳችሁ የፆም ቀኑ የሆነ ጊዜ ፀያፍ ቃልንም አይናገር አይጩህም። አንድ ሰው ከተሰዳደበው ወይም ከተጋደለው እኔ ፆመኛ ሰው ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ታውዳለች። ፆመኛ የሚደስትባቸው ሁለት ደስታ አሉት። ሲያፈጥርም ይደሰታል። ጌታውን የተገናኘ ጊዜም በመፆሙ ይደሰታል።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው በኃላም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።"አቡዳውድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'"ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ" አሉ። እርሳቸውም "በአስቸጋሪ ወቅት ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጂድ እርምጃ ማብዛት፣ አንድ ሰላት ካለቀ በኋላ ሌላ ሶላት መጠበቅ፤ ይኸው ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ) ናቸው።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣ ለናንተ ወርቅና ብር ከመመፅወት የሚበልጥላችሁን ስራ፣ ጠላቶቻችሁን ተገናኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱበት አንገታችሁን ከሚመቱበት ስራችሁም በላጩ የሆነውን ስራ አልነግራችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "አላህን ማውሳት ነው።" አሉ።»ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ከሱለይማን ቢን ሱረድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ተቀምጬ ሳለ ሁለት ሰዎች ይሰዳደባሉ። አንዱ ፊቱ ቀልቷል፣ ደም ስሩ ተገታትሯል። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ "እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።" ለርሱም ሄደው "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ" እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም "እኔ ላይ እብደት አለብኝ እንዴ?" አላቸው።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ለአማኞች እስር ቤት ለከሃዲዎች ጀነት ናት።"»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "መልካም ህልም ከአላህ ነው። መጥፎ ህልም ከሸይጧን ነው። አንዳችሁ የሚፈራውን መጥፎ ህልም የተመለከተ ጊዜ ወደ ግራው ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ያኔ እርሷም አትጎዳውም።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «يَغْفِرُ الله للشَّهيد كُلَّ شيءٍ إلا الدَّين». وفي رواية له: «القَتْل في سَبِيل الله يُكَفِّر كلَّ شيءٍ إلا الدَّين».رواه مسلم
ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ይሉ ነበር: "አላሁመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ፣ ወትቱቃ፣ ወልዓፋፈ፣ ወልጊና" ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ቀናውን መንገድ፣ ጥንቁቅነትን፣ ጥብቅነትንና መብቃቃትን እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «إن العبد لَيَتَكَلَّمُ بالكلمة من رِضْوَانِ الله تعالى ما يُلْقِي لها بَالًا يَرْفَعُهُ الله بها درجاتٍ، وإن العبد لَيَتَكَلَّمُ بالكلمة من سَخَطِ الله تعالى لا يُلْقِي لها بَالًا يَهْوِي بها في جهنم». وعن أبي عبد الرحمن بلال بن الحارث المزني رضي الله عنه : أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «إن الرجل لَيَتَكَلَّمُ بالكلمة من رِضْوَانِ الله تعالى ما كان يظن أن تبلغ ما بَلَغَتْ يكتب الله له بها رِضْوَانَهُ إلى يوم يَلْقَاهُ، وإن الرجل لَيَتَكَلَّمُ بالكلمة من سَخَطِ الله ما كان يظن أن تبلغ ما بَلَغَتْ يكتب الله له بها سَخَطَهُ إلى يوم يَلْقَاهُ».حديث أبي هريرة -رضي الله عنه-: رواه البخاري. حديث بلال المزني -رضي الله عنه-: رواه الترمذي وابن ماجه ومالك وأحمد
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «إنَّ في الجنَّة مائةَ دَرَجَة أعَدَّهَا الله للمُجاهِدين في سَبِيل الله ما بَيْنَ الدَّرَجَتَيْنِ كما بين السماء والأرض».رواه البخاري
عن جابر رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «إن في الليل لساعة، لا يُوَافِقُهَا رجُلٌ مُسلم يَسأل الله تعالى خيرًا من أمْرِ الدنيا والآخرة، إلا أعْطَاه إِياه، وذلك كُلَّ ليلة».رواه مسلم
عن أبي هريرة رضي الله عنه : أن رجلًا أتى النبي صلى الله عليه وسلم يَتَقَاضَاهُ فَأغْلَظَ له، فَهَمَّ به أصحابه، فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «دَعُوه، فإن لِصَاحب الحَقِّ مَقَالا» ثم قال: «أعْطُوهُ سِنًّا مِثْل سِنِّهِ» قالوا: يا رسول الله، لا نَجِدُ إلا أمْثَلَ مِنْ سِنِّهِ، قال: «أعْطُوه، فإن خَيْرَكم أحْسَنُكُم قَضَاء».متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል "አላህ እንዲህ አለ: እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። ለብቻው ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ፤ በህብረት ካወሳኝ ደሞ ከርሱ የተሻለ በሆኑ ህብረቶች ዘንድ አወሳዋለሁ። አንድ ስንዝር ወደኔ ከቀረበ አንድ ክንድ ወደርሱ እቀርባለሁ። አንድ ክንድ ወደኔ ከቀረበ እጅ ሙሉ ወደርሱ እቀርባለሁ። እየተራመደ ወደኔ ከመጣ በሶምሶማ ወደርሱ እመጣለሁ።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሹረይሕ ቢን ሃኒእ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።»ሙስሊም ዘግበውታል።