Hadith for the World
Topic

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

288 hadiths

288 hadiths

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: "لِيُسَلِّمِ الصغيرُ على الكبيرِ، والمارُّ على القاعدِ، والقليلُ على الكثيرِ" وفي رواية: "والراكبُ على الماشي".متفق عليه
ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "መንገድ ተቋርጦብኛልና የምጓጓዝበት እንስሳ ይስጡኝ?" አላቸው። እሳቸውም "የለኝም!" አሉት። ሌላ ሰውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ መጓጓዣ የሚሰጠውን እጠቁመዋለሁ!" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።" አሉ።ሙስሊም ዘግበውታል።
عن علي بن أبي طالب رضي الله عنه مرفوعاً: «إذا انْتَعَل أحدكم فليبدأ باليمين، وإذا نَزَعَ فليبدأ بالشمال، ولْتَكُن اليُمنى أولَهُما تُنْعَل، وآخِرَهُما تُنْزَع».متفق عليه
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ለኩራት ልብሱን የጎተተን ሰው አላህ አይመለከተውም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «من الكبائر شَتْمُ الرجل والديه» قيل: وهل يسبّ الرجل والديه؟ قال: «نعم، يسبّ أبا الرجل فيسبّ أباه، ويسبّ أمّه، فيسبّ أمّه».متفق عليه
ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከዕብ ቢን ዑጅራህ አገኘኝና እንዲህ አለኝ: 'ስጦታ ላበርክትልህን? ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው? እርሳቸውም፦ ‹አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ፤ አልላሁመ ባሪክ ዓላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ። በሉ› አሉን።'" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ውዳሴህን ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው፤ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው ረድዔትን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸውም ረድዔትን አውርድላቸው፡፡ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡”)ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي أمامة رضي الله عنه قال: سمعتُ رسولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم يقولُ: «اقْرَؤُوا القرْآنَ؛ فَإنَّهُ يَأتِي يَوْمَ القِيَامَةِ شَفِيعًا لأَصْحَابِهِ».رواه مسلم
عن أبي ذر الغفاري رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «ألاَ أُخْبِرُكَ بِأَحَبِّ الكَلاَمِ إِلَى اللهِ؟ إنَّ أَحَبَّ الكلام إِلى الله: سبحان اللهِ وبحمدِهِ».رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጀሪር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"ቡኻሪ ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: «والذي نفسي بيده، لو لم تذنبوا، لذهب الله بكم، وجاء بقوم يُذْنِبُونَ، فيستغفرون اللهَ تعالى، فيغفر لهم».رواه مسلم
عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه مرفوعاً: «يُؤْتَى بجهنم يومئذ لها سبعون ألف زِمَامٍ مع كل زمام سبعون ألف ملك يَجُرُّونَهَا».رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱጁድ ውስጥ እንዲህ ይሉ ነበር "አላሁመግፊርሊ ዘንቢ ኩለሁ ዲቀሁ ወጂለሁ፣ ወአወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዐላኒየተሁ ወሲረሁ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ደቂቁንም ትልቁንም፣ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም፣ ግልፁንም፣ ድብቁንም ወንጀሌን ሁሉንም ማረኝ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "الْبَاقِيَاتُ الصَّالِحَاتُ، لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ، وَسُبْحَانَ اللَّهِ، وَاَللَّهُ أَكْبَرُ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاَللَّهِ".رواه ابن حبان والحاكم، أما النسائي فرواه في الكبرى لكن من حديث أبي هريرة
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።