AM
Topic
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት
288 hadiths
ደረጃ ያላቸው ስራዎች
64
ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ
56
ሸሪዓዊ ስነ-ስረዓቶች
67
የዱዓና አዝካር ፊቅህ
62
ቀልብን አርጣቢ ምክሮችና ተግሳጾች
63
288 hadiths
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ። ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለው፤ እርዳታ አይንፈገው፤ አያሳንሰው።" ወደ ደረታቸው እየጠቆሙም ሶስት ጊዜ "አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው።" አሉ። "ሰውዬው ሙስሊም ወንድሙን አሳንሶ መመልከቱ መጥፎ ሠራ ለመባል ይበቃዋል። ሁሉም ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ደሙ፣ ገንዘቡና ክብሩ እርም ነው።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።
ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማ: "በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"
ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «وَاللهِ إني لأَسْتَغْفِرُ اللهَ وأَتُوبُ إليهِ في اليومِ أَكْثَرَ من سَبْعِينَ مَرَّةً».
رواه البخاري
ከአልአገርሪ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي أمامة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم كَانَ إذا رَفَعَ مَائِدَتَهُ، قال: «الحَمْدُ للهِ حَمْدًا كَثِيرًا طَيِّبًا مُبَارَكًا فِيهِ، غَيْرَ مَكْفِيٍّ، وَلَا مُوَدَّعٍ، وَلَا مُسْتَغْنًى عَنْهُ رَبَّنَا».
رواه البخاري
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «لا يُلْدَغُ المؤمنُ من جُحْرٍ واحد مرتين».
متفق عليه
ከጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس رضي الله عنه قَالَ: كُنْتُ أمشي مَعَ رسول الله صلى الله عليه وسلم وَعَلَيْهِ بُرْد نَجْرَانيٌّ غَلِيظُ الحَاشِيَةِ، فأدْرَكَهُ أعْرَابِي فَجَبذَهُ بِرِدَائِهِ جَبْذَة شَديدة، فَنَظَرْتُ إِلَى صَفْحَةِ عَاتِقِ النَّبيِّ صلى الله عليه وسلم وَقَدْ أثَّرَتْ بِهَا حَاشِيَة الرِّدَاءِ مِنْ شِدَّةِ جَبْذَتِه، ثُمَّ قَالَ: يَا مُحَمَّدُ، مُر لِي مِنْ مَالِ اللهِ الَّذِي عِنْدَكَ. فَالتَفَتَ إِلَيْهِ، فَضَحِكَ ثُمَّ أَمَرَ لَهُ بِعَطَاءٍ.
متفق عليه
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: ما عاب رسول الله صلى الله عليه وسلم طعاما قط، إن اشتهاه أكله، وإن كرهه تركه.
متفق عليه
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።" አሉ። "የምናገረው ነገር ወንድሜ ላይ ካለስ (ሀሜት ይባላልን?)" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "የምትናገረው ነገር እሱ ላይ ካለ በርግጥ አምተኸዋል። እሱ ላይ ከሌለ ደግሞ በርግጥም ቀጥፈህበታል።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ابن عمر رضي الله عنهما مرفوعا: «الظلم ظلمات يوم القيامة». عن جابر رضي الله عنهما مرفوعا: «اتقوا الظلم، فإن الظلم ظلمات يوم القيامة، واتقوا الشُّحَ؛ فإنه أَهْلَكَ من كان قبلكم».
حديث ابن عمر -رضي الله عنهما-: متفق عليه. حديث جابر -رضي الله عنه-: رواه مسلم
ከኸውለህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) የአላህ ባሮች ሆይ! ወንድማማቾች ሁኑ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊምን መስደብ አመፀኝነት ነው። መግደሉ ክህደት ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "إذا كنتم ثلاثة فلا يتناجى اثنان دون الآخَر، حتى تختلطوا بالناس؛ من أجل أن ذلك يحُزنه".
متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «كلُّ بني آدم خَطَّاءٌ، وخيرُ الخَطَّائِينَ التوابون».
رواه الترمذي وابن ماجه والدارمي وأحمد
ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ: "ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
Previous page
Page 5 of 12
Next page