Hadith for the World
Topic

ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

288 hadiths

288 hadiths

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።" አቡ ሰዒድም በዚህች ንግግር ተደሰተና እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በድጋሚ ይንገሩኝ!" እርሳቸውም ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉ: "ሌላም አንድ ስራ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ ይደረጋል። በየሁሉም ደረጃ መካከልም ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አቡ ቀታዳህ አንድ ተበዳሪውን ሲፈልገው ከርሱ ተሸሸገ። ከዚያም አገኘው። ተበዳሪውም "እኔ ችግርተኛ ነኝ።" አለው። እርሱም "ወላሂ በል!" አለው። ተበዳሪውም "ወሏሂ!" አለ። አቡቀታዳም እንዲህ አለ: "እኔ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:‐ ‹‹ከትንሳኤ ቀን ችግሮች አላህ እንዲገላግለው ያስደሰተው ሰው ለችግርተኛ ፋታ ይስጥ ወይም ከርሱ ያቅልልለት።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
وعن سالم بن عبد الله بن عمر بن الخطاب رضي الله عنهم عن أبيه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: « نِعْمَ الرَّجُلُ عبد الله، لو كان يُصلِّي من الليل» قال سالم: فكان عبد الله بعد ذلك لا يَنامُ من الليل إلا قليلًا.متفق عليه
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሰህል ቢን ሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዘይድ ቢን ሣቢት - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጋር ሰሑር በላን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ። እኔም (አነስም ለዘይድ) "በአዛንና በሰሑር መካከል ምን ያክል ወቅት ነበር?" አልኩኝ። እርሱም (ዘይድም)፦ "ሃምሳ አንቀፅ የሚቀራበት ያህል" አለኝ።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُما قَالَ: كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي سَفَرٍ، فَرَأَى زِحَامًا وَرَجُلًا قَدْ ظُلِّلَ عَلَيْهِ، فَقَالَ: «مَا هَذَا؟»، فَقَالُوا: صَائِمٌ، فَقَالَ: «لَيْسَ مِنَ البِرِّ الصَّوْمُ فِي السَّفَرِ»، وَفِي لَفْظٍ لِمُسلِمٍ: «عَلَيْكُمْ بِرُخْصَةِ اللهِ الَّذِي رَخَّصَ لَكُمْ».متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና ዘካተል ፊጥርን አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከገብስ ማውጣትን በባሪያውም፣ በነፃውም፣ በወንዱም፣ በሴቱም፣ በህፃኑም፣ በትልቁም ሙስሊም ላይ ግዴታ አደረጉ። ሰዎች ወደ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عائشة وأم سلمة رضي الله عنهما «أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان يُدْرِكُهُ الفجر وهو جُنٌبٌ من أهله، ثم يغتسل ويصوم ».متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾም፣ የዱሓን ሁለት ረከዓ በመስገድና ከመተኛቴ በፊት ዊትር በመስገድ አደራ ብለውኛል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «إذا أقبل الليل من هَهُنا، وأَدْبَرَالنهار من ههنا، فقد أفطر الصائم».متفق عليه
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ። ‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›"»رواه الترمذي والنسائي وأحمد
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች። ይህም አንዳቸው ዉዱእ ሲያደርግ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከሶላት በስተቀር ሳያንቀሳቅሰው ከሶላትም በስተቀር ሌላን ሳይፈልግ ወደ መስጅድ ከመጣ መስጂድ እስኪገባ ድረስ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ልክ ለርሱ ደረጃው ከፍ ይደረግለታል፤ ወንጀሉም ከርሱ ላይ በሷው ይራገፍለታል። መስጂድ የገባ ገዜም በሶላቷ ምክንያት እስከተጠመደ ድረስ ሶላት ውስጥ ነው። አንዳችሁ በሰገደበት ስፍራ ላይ እስከዘወተረ ድረስም ሰዎችን እስካላወከና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላእክቶች በርሱ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ። 'አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው' ይላሉም።'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «ما نهيتكم عنه فاجتنبوه، وما أمرتكم به فأْتُوا منه ما استطعتم، فإنما أَهلَكَ الذين من قبلكم كثرةُ مسائلهم واختلافهم على أنبيائهم».متفق عليه
عن أبي ذر رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم :«عُرِضَتْ عَلَيَّ أعمالُ أُمتي، حَسَنُهَا وسَيِّئُهَا فَوَجَدتُ في مَحَاسِنِ أَعْمَالِهَا الأَذَى يُمَاطُ عَنِ الطَّرِيقِ، ووَجَدتُ في مَسَاوِئِ أَعْمَالِهَا النُّخَاعَةُ تَكُونُ في المَسْجِدِ لا تُدْفَنُ».رواه مسلم