Hadith for the World
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

የአምልኮ ፊቂህ

231 hadiths

231 hadiths

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉበት፤ ውሃ የምናመላልስበትን አንድ ግመል ደግሞ ለኛ ተወልን።" አለች። እርሳቸውም "ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن فَضَالَةُ بنُ عُبَيْدٍ وسلمان الفارسي وعقبة بن عامر الجهني رضي الله عنهم مرفوعاً: «كُلُّ مَيِّتٍ يُخْتَمُ على عَمَلِهِ إلا الُمرَابِطَ في سبيل الله، فإنه يَنْمِي لَهُ عَمَلَهُ يوم القيامة، ويُؤَمَّنُ فتنة القبر».رواه أبو داود والترمذي وأحمد من حديث فضالة -رضي الله عنه
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው፡ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብሏል፦ "ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴትና ህፃናትን መግደልን አወገዙ።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن أبي أوفى رضي الله عنه أَنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم فِي بَعْض أَيَّامه التي لَقِي فيها العدو انتظر، حتى إذا مَالَتِ الشمس قام فِيهم، فقال: «أَيُّها الناس، لا تَتَمَنَّوْا لِقَاء الْعَدُوِّ، وَاسْأَلوا الله الْعافية فَإِذا لَقِيتموهم فَاصْبِرُوا، وَاعلموا أَنَّ الْجَنَّة تحت ظِلال السُّيوف ثُمَّ قَال النَّبِي صلى الله عليه وسلم: اللهمَّ مُنزِلَ الْكتاب، وَمُجْرِيَ السَّحاب، وَهازم الأَحْزاب: اهْزِمهم، وَانصُرنا علَيهم».متفق عليه
ከሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ ረዲየላሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ለአንድ ቀን በአላህ መንገድ ኬላ መጠበቅ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ አንዳችሁ ጀነት ውስጥ ያለው አለንጋ የሚያህል ቦታ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ ባሪያው በአላህ መንገድ ማልዶ መጓዙ ወይም አርፍዶ መጓዙ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጀግንነት ስለሚጋደል፣ ለወገንተኝነት ስለሚጋደልና ለይዩልኝ ስለሚጋደል ሰው ተነስቶ ‹በአላህ መንገድ የተጋደለው የትኛው ነው?› ተብለው ተጠየቁ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم : «ما من مَكْلُومٍ يُكْلَمُ في سبيل الله، إلا جاء يومَ القيامة، وكَلْمُهُ يَدْمَى: اللَّونُ لَوْنُ الدَّمِ، والرِّيحُ رِيحُ المِسْكِ».متفق عليه
عن عَبْد اللهِ بن أبي أوفى رضي الله عنهما قال: «غَزَوْنَا مَعَ رَسُولِ الله صلى الله عليه وسلم سَبْعَ غَزَوَاتٍ، نَأْكُلُ الْجَرَادَ».متفق عليه
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሙጊራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "አንድ ጉዞ ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩና ኹፋቸውን (የቆዳ ካልሲያቸውን) ላወልቅ ዝቅ አልኩ፤ እሳቸውም: ' እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።' አሉኝና በነርሱ ላይ አበሱ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما «أنَّ رسُول الله -صلَّى الله عليه وسلَّم- دَخَل مكَّة مِن كَدَاٍء، مِن الثَنِيَّة العُليَا التِّي بالبَطحَاءِ، وخرج من الثَنِيَّة السُفلَى».متفق عليه
ከዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - እንደተላለፈው: "ዑመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ (ሐጀሩል አስወድ) መጣና ሳመው። እንዲህም አለ: እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن زيد بن عاصم المازني رضي الله عنه قال: (شُكِيَ إلى النبيِّ صلى الله عليه وسلم الرَّجلُ يُخَيَّلُ إِليه أنَّه يَجِد الشَّيء في الصَّلاة، فقال: لا ينصرف حتَّى يَسمعَ صَوتًا، أو يَجِد رِيحًا).متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከእናትችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ። 'አትተሒይያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦይዪባቱ አስ‐ሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ፤ አስ‐ሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስ‐ሷሊሒን፤ አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ትርጉሙም: “ክብርና ልዕልና እንዲሁም ሶላቶችና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው፡፡ አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቶች በእርሶ ላይ ይስፈን ፤ ሰላም በእኛና በአላህ ደጋግ ባሮችም ላይ ይስፈን፤ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡”።)" በሌላ የቡኻሪና ሙስሊም ዘገባ "አላህ እርሱ ሰላም ነው። አንዳችሁ ሶላት ላይ በተቀመጠ ወቅት 'አትተሒይያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦይዪባቱ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ፤ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን' ይበል። ይህንን ያለ ጊዜ በሰማይም ውስጥ ሆነ በምድር ውስጥ የሚገኝ ደግ የአላህ ባሪያ ሁሉ ዱዓው ይደርሰዋል። ቀጥሎ 'አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' ይበል ከዚያም የፈለገውን ዱዓእ መርጦ ያድርግ!"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قال: خَسَفَت الشمس على زمان رسول الله صلى الله عليه وسلم . فقام فَزِعًا، ويخشى أن تكون الساعة، حتى أتى المسجد، فقام، فصلى بأطول قيام وسجود، ما رأيته يفعله في صلاته قطُّ، ثم قال: إن هذه الآيات التي يُرْسِلُهَا الله عز وجل : لا تكون لموت أحد ولا لحياته، ولكن الله يُرْسِلُهَا يُخَوِّفُ بها عباده، فإذا رأيتم منها شيئا فَافْزَعُوا إلى ذكر الله و دُعَائِهِ وَاسْتِغْفَارِهِ.متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): 'አሏሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወሚን ዓዛቢ‐ን‐ናር ወሚን ፊትነቲል መሕያ ወል መማት ወሚን ፊትነቲል መሲሒ‐ድ‐ደጃል' እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።" 'ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' ማለት ነው። በሙስሊም ዘገባ ደግሞ 'አንዳችሁ ከመጨረሻው ተሸሁድ ያጠናቀቀ ጊዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ: ከጀሀነም ቅጣት፣ ከቀብር ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተናና ከመሲሕ ደጃል ክፋት።'ብለዋል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። እኔም የአላህ መልክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁንሎና በተክቢራ እና በፋቲሓ መካከል ዝምታዎን አይቻለሁና ምንድን ነው የሚሉት? አልኳቸው። እርሳቸውም " 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ አልላሁምመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዱ ሚነድደነስ፣ አልላሁምመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ' ነው የምለው" አሉኝ። (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው በኔና በወንጀሌ መካከል አራርቅ! አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፉ እንደሚጠራው እኔንም ከወንጀሎቼ አጥራኝ! አላህ ሆይ በጤዛ፣ በውሃና በበረዶ ከወንጀሎቼ እጠበኝ። ማለት ነው።)»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።